Uncategorized

ደብር ነክ ጉዳዮች

እንደ ተቋም ረበቢስ (irrelevant)ማድረግ

ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሉንድ ከተተከለች እነሆ ወደ ሰላሳ አምስተኛ ዓመቷ እየገሰገሰች ትገኛለች። በእነዚህ ዓመታትም ውስጥ በብዙ ውጣ ወረዶች ማልፏም እውቅ ነው። 

ሆኖም ግን እንደ አሁን ጊዜ ያለ ቅጥ አምባሩ የጠፋበት ከላይ እስከታች ድረስ የተንገላጀጀበት ወቅት ደርሶ አያውቅም። እንደ አሁን ጊዜ በአዋቂ አውቆ አጥፊ መዳፍ ስር ወድቃ ለከፍተኛ የጨቅላ ውጥንቅጥነት (infancy disorder) ተዳርጋ አታውቅም። እንደ አሁን ጊዜ ሆን ተብሎ ደብሪቷን ረበቢስ(irrelevant) በማድረግ የአካባቢ የስበት/ማራኪ መዕከልነቷን (center of attraction) ወስዶ ለሌላ ከድልድዩ ማዶ የማድረግን ጥረት ለማስፈፀም  የማይፈነቀል ድንጋይ እንደዘንድሮ የለም።

እንደ አሁን ጊዜ የሉንድ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የራሷ የሆነ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ወይንም ለመግዛት ምዕመናን እየተዘናጉ እንዲሄዱ ተደርጎ አያውቅም። በአጠቃላይ ደብሪቷ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማንነቷ ተነቃንቆ ከመኖር ወደ አለመኖር ደረጃ ላይ ተሸጋግራ አታውቅም።

በመሆኑም ዝም ስጥ ተብሎ ውጦ ቁልጭ የማይኮንበት ወቅት ላይ በመሆናችን የእውነቱን ፈኖስ ማብራት ግድ ብሏል። የፋኖሱ ማብሪያውም በመንፈስ ታምኖ ከእውነት ጋር አለመቆራረጥ ብቻ ነው

ደብረ  ምጥማቅ ቅድስት ማርያምየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሉንድ                                                                          መጽሔት ቦርድ                                                    

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *