Uncategorized

ደብር ነክ ጉዳዮች

ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሉንድ ላለፉት ከስላሳ ዓመታት በላይ ደርሶባት የማያውቅ ከፍተኛ ችግር ውስጥ በአሁኑ ወቅት ወድቃ ትገኛለች። ችግሮቿም የሚፈልቁት በአዛኛው ከምዕመናኑ ዘንድ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መዋቅራዊ ችግር ነው።

በተለይም ጳጳሱ ትክክለኛ መረጃ ስለማያገኙ፣ ቢያገኙም እውነተኛነታቸውን ለማረጋገጥ ጊዜውም ሆነ ፋታ በማይሰጡ በሀገራዊ ጉዳዮች የመወጠር ችግር ምክንያት አስተዳደርን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያኒቷ የገማንያን መናኸሪያ ሆናለች። በያለበት ቃለ ዓዋዲውን ለማስጠበቅ አልተቻለም። ይህ በመሆኑም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ አንባጓሮው ቅጥ አጥቷል። 

በተለይም ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፍፁም የማይተዋወቁ ግለሰቦች መጠምጠምን አዋጭ ሆኖ ስለታያቸው ምድረ ቀሣጥያን ጥምጥሙን እያስቆነጀ፣ ገበናውን በነጠላም ሆነ በካባ እያብለጨለጨ፣ ውዝዋዜን ያለተሰጦው ተውሶ በመምጣት የአውደ ምህረቱን የድምፅ ማጉያን ነክሶ  እግዚአብሔርን ለማምለክ፣መሥዋዕት ለማቅረብ ለምዕመናኑ ሃይማኖታዊ ትምህርት ለመስጠት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን መክበርያ ነዋይ የማካበቻ መናኸሪያ ለማድረግ ደብሯን ተጣብተዋታል።

በመሆኑም ምዕመናን እነሆ በአሁኑ ጊዜ ለነፍሳቸው የሚሆነውንም ሳያገኙ ምድራዊው ሕይወታቸው ማህበራዊ ግኑኝነታቸው በከፋፍለህ አተረማምሰው አባሲ ጠምጣሚዎች አዕምሮአቸው ቆፈን እንዲይዘው ተደርጓል።ምዕመናንም ይህን የጠምጣሚ የአዕምሮ ቆፈን የማስያዣ አካሄድን ለመግታትና ስንሰለቱንም በጣጥሶ ቃለ ዓዋዲያዊ እርምጃ ለመውሰድም የእስከ አሁኑ ይበቃል ከእንግዲህ አለቀ ደቀቀ ብለው በመነሳት ጠምጣሚውን ጥምጥሙን በሊቃውንቱ አስፈትሾ መዐልም መሆኑን ማረጋገጥ። ሆኖ ካልተገኘ   ሥእበት ከተገኘበት ቢያንስ ከመቅደሷ እና ከአውደ ምህረቱ አካባቢ እንዳይደርስ እውነተኞቹ አባቶች እንዲመክሩበት ለማድረግ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ወደ ተግባር ተሽጋግረዋል።

ይህንንም በተጭባጭ ለመተግበር በቅርቡ ምን ይደረግ በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ሊቃውንቱን ማዕከል ያደረገ ስብሰባ/ጉባኤ ጠርተው ሊያወያዩ ወስነው ለመንደርደርያ ፣ለመወያያ የሚሆነውን ጥናታዊ ጽሁፍ በሊቃውንቱ ሙሉ ተሳትፎ የተዘጋጀ በቅርቡ ለምዕመናን አሰራጭተው ሁሉም ተመልክቶት ወደ ጉባኤው /ስብሰባው አንዲመጣ እንደሚያደርጉ ዜናው ደርሶናል። መጽሔት በርዱም በዚህ ተግባር ሊተባበራቸው ወስኖ ልዩ አምድ ስጥቷቸዋል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ሉንድ  !!                                                                                                               መጽሔት ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *