Discussion Forum

ስለ ደብረ ምጥማቅ ዝም፣ ፀጥ አንልም። እውነቷ እንደሚያበራ ፋኖስ እስኪወጣ ድረስ !!!

እንደ ተቋም ረበቢስ (irrelevant)ማድረግ

ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሉንድ ከተተከለች እነሆ ወደ ሰላሳ አምስተኛ ዓመቷ እየገሰገሰች ትገኛለች። በእነዚህ ዓመታትም ውስጥ በብዙ ውጣ ወረዶች ማልፏም እውቅ ነው። 

ሆኖም ግን እንደ አሁን ጊዜ ቅጥ አምባሩ የጠፋበት ሁኔታ ላይ ወድቃ አታውቅም። ከላይኛው መዋቅር እስከ ታችኛው ድረስ አስተዳደራዊ መንዘላዘል ደርሶ አያውቅም። እንደ አሁን ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቷ በአዋቂ አውቆ አጥፊ መዳፍ ስር ወድቃ ለከፍተኛ የጨቅላ ውጥንቅጥነት() ተዳርጋ አታውቅም። እንደ አሁን ጊዜ ሆን ተብሎ  ደብሪቷን ረበቢስ (Irrelevant)ለማድረግ የተሰራበት ጊዜ ኖሮ አያውቅም። እንደ አሁን ጊዜ ሆን ተብሎ የደብረ ምጥማቅን የአካባቢ የስበት መዕከልነቷን (center of attraction) ወስዶ ለሌላ ከድልድዩ ማዶ የማድረግን ጥረት በአደባባይ የተፈፀመበት ጊዜ ኖሮ አይውቅም።እንደ አሁን ጊዜ ለስህተት ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚደረግ መጥፎ ድርጊት ሌሎችን በተለይም ምዕመናንን ተጠያቂ የማድረግ(defiant behavior) ፣ሃላፊነት ያለመውሰድ ብልጣብልጥነት ተንሰራፍቶ አያውቅም። እንደ አሁኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በገዛ ደሙ ያገኛት የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ምጥማቅ የበላይ ተንከባካቢ አጥታ  ዝቡሕ ሆና የወዓርያን መጨፈሪያ መድረክ ሆና አታውቅም።

በሌላ ጎኗ ይበላ ከሚያሰኝ አንፅር ደግሞ እንደ አሁን ጊዜ ምዕመናን ካለ ፈጣሪ ብለው ኪሣቸውን ሳይቆጥቡ እጃቸውን ዘርግተው ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ወይንም ለመግዛት  ተነሳስተው አያውቁም። ሆኖም ግን የሰኔና ሰኞ ግጥመት እንዲሉ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግልፅነት ሳይኖር ሁሉ ነገር ከድልድዮ ማዶ ተድበስብሶ ደብረ ምጥማቅ ሉንድ ረበቢስ (irrelevant) እንድትሆን እየተደረገ ነው። በአጠቃላይ ደብሪቷ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማንነቷ ተነቃንቆ ከመኖር ወደ አለመኖር ደረጃ ላይ እንደዚህ ጊዜ ተሸጋግራ አታውቅም።

ከዚያም አልፎ ሉንድ የራሷ የሆነ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ወይንም ለመግዛት ረጅም ጉዞ ተጉዛ ቀላል ተብሎ የማይገመት ጉዞ እንደተጓዘች የአደባባይሚስጥር ነው።በእርግጥ የዚህ የጉዞ ውጤት እንደሚነገረው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ከድልድዩ ተሻግሮ ወደዚያ እንዲቋጠር ተደርጓል ተብሏል። እሰየው ነው።ለተዋሕዶ እስከሆነ ድረስ ከድልድዩ ማዶ ሆነ ወዲህ ሁሉም ለፅድቅ ነው። ለፅድቅ የማይሆነው ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ማሰሪያ ሳይበጅላቸው ሲቀር ነው፡

፩ኛ:- ለፅድቅ የማይሆነው ሆን ተብሎ ሉንድን ረበቢስ (irrelevant) የማድረጉ ዘጭ እንቦጭ ማለቱ                  በቀጥታ ቆሞ ሉንድ ወደ ቀድሞ ይዞታዋ እንድ ትመለስ ሳይደረግ ሲቀር ነው።                                ፪ኛ:-  በሹመት መንበሽበሽ ደረጃ የተደረገው የጭቅላ ውጥንቅጥነት  ታርሞ በቃለ ዓዋዲው                              መሰረት  ሕጋዊ፣ ታማኝ የሰበካ ጉብዔ መኖር ሳይረጋገጥ ሲቀር ነው።

በድርጅታዊ አሰራር መሰረት ሉንድ (Lund, Sweden) እና ኮፕንሃገን  (Copenhagen, Denmark) ሁለት የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ናቸው። እንዲህም ሆነው እያሉ ሁለቱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በሉንድ ደብረ ምጥማቅ መዋቀራዊ መዕከል አማካኝነት ተጋግዘው እና ተፈቃቅደው በምዕመን ቅንነት እና መልካም አሳቢነት ደረጃ ለረጅም ዓመታት አብረው ሊሰሩ ችለዋል።

ሊሰሩ የቻሉበትም መሰረታዊው ምክንያት የሉንድ ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ላለፈት ሰላሳ ዓመታት ለኮፕንሀገን(Copenhagen) ምዕመናን አገልግሎቷን በመሰጠት በማበረታታት ያልተቆጠበ እርዳታዋንም በማድረጓም ጭምር ነው። በተለይም ላለፉት አራት ዓመታት ለአንድ የኮፕንሀገን(Copenhagen) ካህን የሙሉ ሰዓት ስራ በመስጠ ካህኑን ከምዕመናን ጋር በማገናኘት የስኮነ ምዕመናን ለሚሰራው/ለሚገዛው ቤተ ክርስቲያን ወጪ ወሳኙን ድርሻ አንዲሰበሰብ አድርጋለች። ።

ይህን ያክል ከተባለ ዘንዳ ይህ የሁለት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ትብብር በየአካባቢው ላሉ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተምሣሌ ሊሆን የሚገባው መልካም ተግባር ነው። ሆኖም ግን ይህም ተምሳሌነት ዘላቂነትና ችግር አልባ ሆኖ ሊዘልቅ የሚችለው ውሎ ሳያድር ድብ ብቆሽ ሳይኖር ሕጋዊነት እና ግልፅነትን ሲቀዳጅ ብቻ ነው ።

በመሆኑም ከወዲሁ የንብረት ባለቤትነት ስርዓቱ በግልፅ መቀመጥ ይገባዋል። የባለቤትነት ጽንሰ ሀሳብ በግልፅ ተመርምሮ በዙሪያው ያሉትን ህጋዊና አሰራራዊ ገጽታዎች በድንብ አለመሸፋፈን መገለፅ አለባቸው።  ከባለቤትነት ጋር በተያያዘ ነገሮች በብርቱ ውስብስብ ናቸው። ውስብስብነትንም ሊያመጣ የሚችለው መሰረታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ሳይመለሱ ወይንም ግልፅ ሳይሆኑ ሲቀሩ ነው።ልክ በ አሁኑ ሰዓት በሉንድ እና በኮፕንሀገን(Copenhagen) መካከል ያለው ደካም ጎን ቤተ ክርስቲያን ያለው ማን ነው? ግለሰብ ነው ወይስ ቡድን? የሚለው ግልፅነት ይጎድለዋል።አሊያ አበው የሚተርኩት “በጨው ደንደስ በርበሪ ተወደስ” እንዳይሆን። ይህ ጉዳይም በብልጣብልጥነት ሁሉም ለቤተ ክርስቲያን እስከሆነ ድረስ ችግር የለውም የሚል እንደማይጠፋ ይገመታል። ለዚህ መልሱም ይህ የግልፅነት ጥያቄ በመሆኑ ወደ ጎን ማድረግ የሚቻል አይደለም ነው።

ይህ ጥያቄ በግለሰብ ደረጃ የሚታይ ቢሆን ኖሮ ችግር የለውም ነበር። ነገርግን እየተነሳ ያለው ጉዳይ የታቦት ገንዘብ ጉዳይ ነው። የታቦት ገንዘብ ደግሞ የታቦት ነው።ታቦት ደግሞ የእግዚአብሄር ማደርያ ነው። የሕዝብ መባረኪያ ነው። በመሆኑም ለታቦት ስግደትና ክብር መስጠት እንጂ ሣንቲም ወዲህ ሣንቲም ወዲያ በሚል የመነታረኪያ የመጠራጠርያ ስፍራ መሆን የለበትም። ይህን ማድረግም ኃጢዓትና መቅፀፍትን ሊያስከትል ይችላል። ይህ እንዳይከሰት ፍቱህ መድሀኒቱ የሚመለከታቸው ወገኖች ግልጽ ሲሆኑ ብቻ ነው። ለዚህ ነው ትልቁ ሃላፊነት በኮፕንሀገኑ(Copenhagen) ካህን ይባል ወይ ኮሚቴ ላይ ትልቁ ሃላፊነት የሚወድቀው።

ለችግሩ አለመፈጥር መድሐኒት የሚሆነው ከወዲሁ በግልፅ የባለቤትነት ይዞታው ጥያቄ በግልፅ ሲመለስ ነው። ይኸውም ሕጋዊ ባለቤቱ ማን ነው  :—

         ባለቤቱ ሲኖዶሱ ነው?
         ባለቤቱ በኤጲስ ቆጶስ ሥልጣን ሥር ያለው  የስካንድኔቪያ የቤተ ክህነት ሀገረ ስብከት ነው?
         ባለቤቱ በአስተዳዳሪ በአንድ ግለሰብ ካህን የሚመራው የአጥቢያው ስበካ ጉባኤ ነው?
         ባለቤቱ የአንድ አጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ኗሪ የተዋሕዶ ማሕበረሰብ ነው?
         ባለቤቶቹ ትብብር የፈጠሩት የአጥቢያዎች ጥምር የሆኑት የተዋሕዶ ማሕበረሰብ ናቸው?           (ለምሳሌ ሉንድና ኮፕንሀገን)  ወዘተ ወዘተ ለሚሉት  ጥያቄዎች መልስ መሰጠት አለበት።

በመሆኑም ዝም ሰጥ ተብሎ ውጦ ቁልጭ የማይኮንበት ወቅት ላይ መደረሱን በመረዳት የመግባቢያውን ሰነድ እንደ ፋኖሱ መብራት ቦግ አድርጎ በማሳየት በብዙ የአውሮፓ ሀገራት፣በአሜሪካ እንዲሁም በሌሎች ሃገራት የደረሱትን  የባለቤትነትጥያቄ ንትርኮች ከወዲሁ በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀረት መነሳት ግድ   ነው።                                                                                                                                                                                           ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ሉንድ  !!!    መጽሔት ቦርድ                                                                

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *